1 ቆሮንቶስ 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዘማውያን ጋር አንድ እንዳትሆኑ በዚህ መልእክት ጻፍሁላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሴሰኞች ጋራ እንዳትተባበሩ በመልእክቴ ጽፌላችሁ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመልእክቴ ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ ጻፍሁላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በፊት በጻፍኩላችሁ መልእክት ከአመንዝራዎች ጋር አትተባበሩ ብያችሁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ በመልእክቴ ጻፍሁላችሁ። |
የዚህ ዓለም ዝሙት ብቻ አይደለም፤ ቀማኞችና ዘራፊዎች፥ ጣዖትን የሚያመልኩ ደግሞ አሉ፤ ያለዚያስ ከዚህ ዓለም ልትለዩ ይገባል።
እንግዲህ ለአዲስ ቡሆ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ ከእናንተ አርቁ፤ ገና ቂጣ ናችሁና፤ ፋሲካችን ክርስቶስ ተሠውቶ የለምን?
ተጠራጣሪዎች አትሁኑ፤ ወደማያምኑ ሰዎች አንድነትም አትሂዱ፤ ጽድቅን ከኀጢአት ጋር አንድ የሚያደርጋት ማን ነው? ብርሃንንስ ከጨለማ ጋር የሚቀላቅል ማን ነው?
ስለዚህም “ከመካከላቸው ተለይታችሁ ውጡ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩሳንም አትቅረቡ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ።
ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።