Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እን​ግ​ዲህ ለአ​ዲስ ቡሆ ትሆኑ ዘንድ አሮ​ጌ​ውን እርሾ ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ ገና ቂጣ ናች​ሁና፤ ፋሲ​ካ​ችን ክር​ስ​ቶስ ተሠ​ውቶ የለ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አሁን ያለ እርሾ እንደ ሆናችሁ ሁሉ አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፤ የፋሲካ በጋችን የሆነው ክርስቶስ ተሠውቷልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እንግዲህ እርሾ እንደሌለበት እንደ አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ፥ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 አሁን እንደ ሆናችሁት ሁሉ እርሾ እንደሌለበት እንደ አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፤ የፋሲካችን በግ የሆነው ክርስቶስ ተሠውቶአል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 5:7
19 Referencias Cruzadas  

የቀ​ድሞ ጠባ​ያ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ ይህ​ንም ስሕ​ተት በሚ​ያ​መ​ጣው ምኞት ስለ​ሚ​ጠ​ፋው ስለ አሮ​ጌው ሰው​ነት እላ​ለሁ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ዮሐ​ንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን አይቶ እን​ዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ።


በታላቅም ድምፅ “የታረደው በግ ኀይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል” አሉ።


“ሰባት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም ቀን እር​ሾ​ውን ከቤ​ታ​ችሁ ታወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን አን​ሥቶ እስከ ሰባ​ተ​ኛው ቀን እርሾ ያለ​በ​ትን እን​ጀራ የሚ​በላ ነፍስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ተለ​ይቶ ይጥፋ።


ኅብ​ስቱ አንድ እንደ ሆነ እን​ዲሁ እኛም ብዙ​ዎች ስን​ሆን አንድ አካል ነን፤ ሁላ​ችን ከአ​ንድ ኅብ​ስት እን​ቀ​በ​ላ​ለ​ንና።


የፋ​ሲ​ካም የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበር፤ ጊዜ​ዉም ስድ​ስት ሰዓት ያህል ነበር፤ ጲላ​ጦ​ስም አይ​ሁ​ድን፥ “እነሆ፥ ንጉ​ሣ​ችሁ” አላ​ቸው፤


የፋሲካን በግ በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ “ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ?” አሉት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ሲሄድ አይቶ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ” አለ።


በውጭ ያሉ​ትን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ ይቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ልም፤ ክፉ​ውን ከእ​ና​ንተ አርቁ።


ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”


እር​ሱ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ም​ነት የሚ​ገኝ፥ በደ​ሙም የሆነ ማስ​ተ​ስ​ረያ አድ​ርጎ አቆ​መው፤ ይህም ከጥ​ንት ጀምሮ በበ​ደ​ሉት ላይ ጽድ​ቁን ይገ​ልጥ ዘንድ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios