La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ምን አግ​ዶኝ፥ በውጭ ባለው ላይ እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ? እና​ን​ተስ በው​ስጥ ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ፈር​ዳ​ችሁ ቅጡ​አ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባሉት ሰዎች ላይ ለመፍረድ እኔን ምን አግብቶኝ? በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉት ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በውጭ ባሉ ሰዎች ላይ መፍረድ ምን አግዶኝ? በውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከክርስቲያናዊ ማኅበር ውጪ ባሉት ሰዎች ላይ ለመፍረድ እኔ ማን ነኝ? በክርስቲያናዊ ማኅበር ውስጥ ስላሉት ሰዎች ጉዳይ እናንተስ መፍረድ ትችሉ የለምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በውጭ ባሉ ሰዎች ላይ መፍረድ ምን አግዶኝ? በውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን?

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 5:12
8 Referencias Cruzadas  

እንዲህም አላቸው “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን፥ ‘አይተው እንዲያዩ እንዳይመለከቱም፤ ሰምተውም እንዲሰሙ እንዳያስተውሉም፤ እንዳይመለሱ ኀጢአታቸውም እንዳይሰረይላቸው’ ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንተ ሰው፥ በእ​ና​ንተ ላይ አካ​ፋ​ይና ዳኛ አድ​ርጎ ማን ሾመኝ?” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእኔ መን​ግ​ሥት ከዚህ ዓለም አይ​ደ​ለ​ችም፤ መን​ግ​ሥ​ቴስ በዚህ ዓለም ብት​ሆን ኖሮ ለአ​ይ​ሁድ እን​ዳ​ል​ሰጥ አሽ​ከ​ሮች በተ​ዋ​ጉ​ልኝ ነበር፤ አሁ​ንም መን​ግ​ሥቴ ከዚህ አይ​ደ​ለ​ችም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ዘመ​ኑን እየ​ዋ​ጃ​ችሁ ከሃ​ይ​ማ​ኖት ወደ ተለዩ ሰዎች በማ​ስ​ተ​ዋል ሂዱ።


በዲያቢሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቅ፥ በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር ሊኖረው ይገባዋል።