እነሆ ይህ የመንገዱ ክፍል ነው፤ የቀሩትንም ነገሮቹን እንሰማለን፤ በሚያደርግበትስ ጊዜ የነጐድጓዱን ኀይል የሚያውቅ ማን ነው?”
1 ቆሮንቶስ 13:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየገጹ ጥቂት ጥቂት እናውቃለንና፤ ጥቂት ጥቂት ትንቢትም እንናገራለንና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም የምናውቀው በከፊል ነው፤ ትንቢት የምንናገረውም በከፊል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም የምናውቀው በከፊል ነው፤ ትንቢት የምንናገረውም በከፊል ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምናውቀውም ሆነ ትንቢት የምንናገረው በከፊል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና፤ |
እነሆ ይህ የመንገዱ ክፍል ነው፤ የቀሩትንም ነገሮቹን እንሰማለን፤ በሚያደርግበትስ ጊዜ የነጐድጓዱን ኀይል የሚያውቅ ማን ነው?”
ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
አሁን ግን ታወቀኝ፤ በግልጥም ተረዳኝ፤ በመስታወትም እንደሚያይ ሰው ዛሬ በድንግዝግዝታ እናያለን፤ ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ አሁን በከፊል፥ ኋላ ግን እንደ ተገለጠልኝ መጠን ሁሉን አውቃለሁ።
ነገር ግን መጽሐፍ፥ “ዐይን ያላየው፥ ጆሮም ያልሰማው፥ በሰውም ልቡና ያልታሰበ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ነው።” ብሎ የለምን?
ከቅዱሳን ሁሉ ለማንስ ለእኔ የማይመረመረውን የክርስቶስን ባለጸግነት ለአሕዛብ አስተምር ዘንድ ይህን ጸጋ ሰጠኝ።
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።