1 ቆሮንቶስ 12:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን ግን እግዚአብሔር የአካላችንን ክፍል በሰውነታችን ውስጥ እርሱ እንደ ወደደ እየራሱ አከናውኖ መደበው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ እያንዳንዱን በአካል ውስጥ መድቧል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ የአካል ክፍሎችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ፈለገው እያንዳንዱን የአካል ክፍል በአካል ውስጥ ተገቢ ስፍራውን ይዞ እንዲገኝ አድርጎታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ ብልቶችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል። |
በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እናገራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች፤ የመከርሁትንም ሁሉ አደርጋለሁ እላለሁ።
ሁሉም አንድ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ “አቤቱ! አንተ እንደ ወደድህ አድርገሃልና ስለዚህ ሰው ነፍስ አታጥፋን፤ ንጹሕ ደምንም አታድርግብን።” አሉ።
በዚያች ሰዓትም ጌታችን ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ደስ አለው፤ እንዲህም አለ፥ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከዐዋቂዎችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለገለጥኸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲሁ ሆኖአልና።
በተሰጠኝ በእግዚአብሔር ጸጋ ሁላችሁም እንዳትታበዩ እነግራችኋለሁ፤ ራሳችሁን ከዝሙት የምታነጹበትን ዐስቡ እንጂ ትዕቢትን አታስቡ፤ ሁሉም እንደ እምነቱ መጠን እግዚአብሔር እንደ አደለው ይኑር።
ለከበረው የአካላችን ክፍል ክብርን አንሻለትም፤ እግዚአብሔር ግን ሰውነታችንን አስማምቶታል፤ ይልቁንም ታናሹን የአካል ክፍል አክብሮታል።
እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የሾማቸው አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም መምህራንን፥ ከዚህም በኋላ ተአምራትና ኀይል ማድረግ የተሰጣቸውን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ሀብት የተሰጣቸውን፥ የመርዳትም ሀብት የተሰጣቸውን፥ የመምራትና ቋንቋን የመናገር ሀብት የተሰጣቸውን ነው።
እንግዲህ ጳውሎስ ምንድን ነው? አጵሎስስ ምንድን ነው? እነርሱስ በቃላቸው የአመናችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ ለእያንዳንዱም እግዚአብሔር እንደ ሰጠው ነው።