1 ቆሮንቶስ 10:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ምን እንላለን? ለጣዖታት የሚሠዋ መሥዋዕት ከንቱ ነው፤ ጣዖቶቻቸውም ከንቱ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ፣ ለጣዖት የተሠዋ ነገርም ሆነ ጣዖቱ ራሱ ዋጋ ያለው ነገር ነው ማለቴ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ምን እላለሁ? ለጣዖት የተሠዋ የሚረባ ነገር ነው? ወይስ ጣዖት የሚረባ ነገር ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ ይህን ስል ለጣዖት የተሠዋ ሥጋ የሚረባ ነገር ነው ማለቴ ነውን? ወይስ ጣዖት የሚረባ ነገር ነው ማለቴ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ምን እላለሁ? ለጣዖት የተሠዋ ምናምን ነው እላለሁን? ወይስ ጣዖት ምናምን እንዲሆን እላለሁን? |
አሁን ግን እንደምታዩትና እንደምትሰሙት ይህ ጳውሎስ ኤፌሶንን ብቻ ሳይሆን መላውን እስያን አሳተ፤ ብዙ ሕዝብንም መለሰ፤ በሰው እጅ የሚሠሩትንም ሁሉ አማልክት አይደሉም አላቸው።
ትንቢት ብናገር፥ የተሰውረውን ሁሉ፥ ጥበብንም ሁሉ ባውቅ፥ ተራራ እስከ ማፍለስ የሚያደርስ ፍጹም እምነትም ቢኖረኝ ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
ለጣዖታት የተሠዋውን ስለመብላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደሆነ፥ ከአንድ እግዚአብሔርም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
እነሆ እናንተ ስላገበራችሁኝ በመመካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእኔማ በእናንተ ዘንድ ልከብርና እናንተም ምስክሮች ልትሆኑኝ ይገባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢምንት ብሆንም ዋናዎቹ ሐዋርያት ሁሉ ከሠሩት ሥራ ያጐደልሁባችሁ የለምና።
አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በጣዖቶቻቸውም አስቈጡኝ፤ እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ በማያስተውል ሕዝብም አስቈጣቸዋለሁ።