አባታቸውንም በዚያች ሌሊት ደግሞ ወይን አጠጡት፤ ታናሺቱም ገብታ ከአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛም ስትነሣም አላወቀም።
1 ቆሮንቶስ 10:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱን ያገኛቸው ይህ ሁሉ ነገር በኋላ ዘመን ለምንነሣው ለእኛ ትምህርትና ምክር ሊሆነን ምሳሌ ሆኖ ተጻፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ሁሉ ምሳሌ ይሆን ዘንድ በእነርሱ ላይ ደረሰ፤ የዘመናት ፍጻሜ የደረሰብንን እኛን ለማስጠንቀቅም ተጻፈ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ሁሉ ነገር እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፤ የተጻፈው ግን በዘመናት መጨረሻ ለምንገኘው ለእኛ ተግሣጽ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሁሉ ነገር የደረሰባቸው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ እንዲሆን ነው፤ የተጻፈውም በዘመናት መጨረሻ ላይ ለምንገኘው ለእኛ ትምህርት እንዲሆነን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ። |
አባታቸውንም በዚያች ሌሊት ደግሞ ወይን አጠጡት፤ ታናሺቱም ገብታ ከአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛም ስትነሣም አላወቀም።
በቍጣዬና በመቅሠፍቴ በተበቀልሁሽ ጊዜ በዙሪያሽ በአሉ በአሕዛብ ዘንድ ትጨነቂያለሽ፤ ትደነግጫለሽም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ነገር ግን ወንድሞቻችን እንዲህ ይቀናል፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ሁሉ ሊያልፍ ቀርቦአልና፤ አሁንም ያገቡ እንዳላገቡ ይሆናሉ።
ይህን የሚለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይደለምን? የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ፥ የሚያበራይም እንዲካፈል በተስፋ ሊያበራይ ስለሚገባው በእውነት ስለ እኛ ተጽፎአል።
ሌሎች ልማድ አድርገው እንደ ያዙት ማኅበራችንን አንተው፤ እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።
ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።