1 ዜና መዋዕል 9:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየሰንበቱም ያዘጋጁ ዘንድ ቀዓታዊው በንያስና ወንድሞቻቸው በገጹ ኅብስት ላይ ሹሞች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየሰንበቱ ለሚዘጋጀው ገጸ ኅብስትም ኀላፊነቱ የተሰጠው ከቀዓታውያን ወንድሞቻቸው መካከል ለአንዳንዶቹ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወንድሞቻቸውም ከቀዓታውያን አንዳንዶቹን በየሰንበቱ የተቀደሰውን ኅብስት እንዲያዘጋጁ ሹሞች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀዓት ጐሣ አባሎች አንዳንዶቹ ለቤተ መቅደስ የሚሆን ኅብስት በየሰንበቱ የማዘጋጀት ኀላፊነት ነበረባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበሰንበቱም ያዘጋጁ ዘንድ ከወንድሞቻቸው ከቀዓታውያን አንዳንዱ በገጹ ኅብስት ላይ ሹሞች ነበሩ። |
ለቀዓትም የእንበረም ወገን፥ የይስዓር ወገን፥ የኬብሮንም ወገን፥ የአዛሔልም ወገን ነበሩ፤ የቀዓት ወገኖች እነዚህ ናቸው።