ገብተውም በከተማው በር ጮኹ፤ እንዲህም ብለው ተናገሩ፥ “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ገባን፤ እነሆም፥ ፈረሶችና አህዮች ታስረው፥ ድንኳኖችም ተተክለው ነበር እንጂ ያገኘነው አልነበረም፤ የሰውም ድምፅ አልነበረም።”
1 ዜና መዋዕል 9:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ አራቱ ኀያላን ሰዎች ለአራቱ በሮች ኀላፊዎች ነበሩ። ሌዋውያንም በእግዚአብሔር ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ የተሾሙ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌዋውያን የነበሩት አራቱ የበር ጠባቂ አለቆች ግን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚገኙትን ክፍሎችና ግምጃ ቤቶች በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሌዋውያንም የነበሩ አራቱ የጠባቂዎች አለቆች በሥራቸው ታማኞች ነበሩ፤ በጌታም ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ ተሹመው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አራቱም ሌዋውያን የዘበኞች አለቆች ሲሆኑ እነርሱም ሙሉ ሥልጣን ያላቸው ነበሩ፤ እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ላሉት ክፍሎችና በውስጣቸውም ለሚቀመጡ ዕቃዎች ኀላፊዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሌዋውያንም የነበሩ አራቱ የበረኞች አለቆች ዘወትር በሥራቸው ይቀመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ ነበሩ። |
ገብተውም በከተማው በር ጮኹ፤ እንዲህም ብለው ተናገሩ፥ “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ገባን፤ እነሆም፥ ፈረሶችና አህዮች ታስረው፥ ድንኳኖችም ተተክለው ነበር እንጂ ያገኘነው አልነበረም፤ የሰውም ድምፅ አልነበረም።”
ለሌዋውያን፥ ለመዘምራንና ለበረኞቹ እንደ ሕጉ የተሰጣቸውን የእህሉን ቍርባንና ዕጣኑን፥ ዕቃዎቹንም፥ የእህሉንና የወይኑን፥ የዘይቱንም ዐሥራት፥ ለካህናቱም የሆነውን ቀዳምያቱን አስቀድሞ ያስቀመጡበትን ታላቅ ዕቃ ቤት አዘጋጅቶለት ነበር።
“ወደ ሬካባውያን ቤት ሄደህ ተናገራቸው፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት አምጥተህ ከክፍሎቹ ወደ አንዲቱ አግባቸው፤ የወይን ጠጅም አጠጣቸው።”
ወደ ውስጠኛው አደባባይም አገባኝ፤ እነሆም በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ዕቃ ቤቶችና ወለል ነበሩ፤ በወለሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።