1 ዜና መዋዕል 9:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አስቀድሞም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ አለቃቸው ነበረ። እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቀድሞ ጊዜ የበር ጠባቂዎቹ አለቃ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ነበረ፤ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋራ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስቀድሞም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ አለቃቸው ነበረ፤ ጌታም ከእርሱ ጋር ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀደም ሲል የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ እነርሱን ይቈጣጠር ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አስቀድሞም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ አለቃቸው ነበረ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ። |
ጌታውም እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ።
የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱ ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፤ የድንኳኑንም መድረክ ይጠብቁ ነበር። አባቶቻቸውም የእግዚአብሔርን ሰፈር መግቢያ ይጠብቁ ነበር።
እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፤ እንዲህ ሲል፥ “በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ይህ ለአንተ ምልክት ይሆንሃል፤ ሕዝቡን ከግብፅ በአወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታመልካላችሁ” አለው።
ሙሴም ከየነገዱ አንድ ሺህ ከሠራዊታቸውና ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሐስ ጋር ሰደደ፤ ንዋያተ ቅድሳቱና ምልክት መስጫ መለከቶችም በእጆቻቸው ነበሩ።
የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት በጣፋጩም ዕጣን ላይ ፥ ሁልጊዜም በሚቀርበው በእህሉ ቍርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ሹም ነው፤ ድንኳኑን ሁሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ መቅደሱንና ዕቃውን ይጠብቃል።”
በምስክሩ ድንኳን ዘንድ ባለው ሥራቸው ሁሉ የሜራሪ ልጆች ወገኖች አገልግሎት ይህ ነው፤ እነርሱም ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከኢታምር እጅ በታች ይሆናሉ።”
የእስራኤልም ልጆች በገለዓድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ የካህኑ የአሮንን ልጅ የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ላኩ።
ከብላቴኖቹም አንዱ መልሶ፥ “እነሆ፥ መልካም አድርጎ በገና ሲመታ የቤተ ልሔሙን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፤ ሰውየውም ጠቢብ፥ ተዋጊም ነው፤ በነገርም ብልህ፥ መልኩም ያማረ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው” አለ።