1 ዜና መዋዕል 7:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴት ልጁም ስም ሲአራ ነበረ፤ በዚያም በቀሩት ታችኛውንና ላይኛውን ቤትሖሮንን ሠራ የኡዛንም ልጁ ሠይራ ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴት ልጁ ስሟ ሲአራ ይባላል፤ እርሷም የታችኛውንና የላይኛውን ቤትሖሮንንና ኡዜንሼራን የተባሉትን ከተሞች የቈረቈረች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴት ልጁም ታችኛውንና ላይኛውን ቤት-ሖሮንንና ኡዜን-ሼራን የሠራች ሲኦራ ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤፍሬም፥ ሼኢራ ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ወለደ፤ እርስዋም የላይኛውንና የታችኛውን ቤትሖሮን፥ እንዲሁም ዑዜንሼኢራ ተብለው የሚጠሩትን ከተማዎች አሠራች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴት ልጁም ታችኛውንና ላይኛውን ቤትሖሮንንና ኡዜንሼራን የሠራች ሲአራ ነበረች። |
ደግሞም ቅጥርና መዝጊያ፥ መወርወሪያም የነበራቸውን የተመሸጉትን ከተሞች ላይኛውን ቤትሖርን፥ ታችኛውንም ቤትሖርን ሠራ።
ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤቶሮን ዳርቻ ድረስ ይወርዳል፤ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
የኤፍሬምም ልጆች ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፤ የርስታቸው ድንበር ከአጣሮትና፥ ከኤሮሕ ምሥራቅ ከጋዛራ እስከ ላይኛው ቤቶሮን ድረስ ነበረ፤