1 ዜና መዋዕል 6:62 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጌርሶን ነገድ በየጐሣቸው ከይሳኮር፣ ከአሴር፣ ከንፍታሌምና በባሳን ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ ድርሻ ላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጌርሾን ጐሣም ከይሳኮር፥ ከአሴር፥ ከንፍታሌምና በባሳን ካለው ከምሥራቅ ምናሴ ግዛቶች በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ለየቤተሰቡ ተመድበው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ። |
ያችም ሴት ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ ሙሴም፥ “በሌላ ምድር መጻተኛ ነኝ” ሲል ስሙን ጌርሳም ብሎ ጠራው። ዳግመኛም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ኤልኤዜር አለው፤ የአባቴ ፈጣሪ ረዳቴ ነው ሲል።
ድንበራቸውም ወደ ታቦርና ወደ ሰሌም፥ በምዕራብ በኩል ወደ ቤተሳሚስ ይደርሳል፤ የድንበራቸው መውጫም ዮርዳኖስ ነበረ፤ ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸውም።
ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተሰጡአቸው።