በዘመኑም የአሶር ንጉሥ ፎሐ በምድሪቱ ላይ ወጣ፤ ምናሔምም የፎሐ እጅ ከእርሱ ጋር እንዲሆን አንድ ሺህ መክሊት ብር ሰጠው።
1 ዜና መዋዕል 5:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባቶቻቸውንም አምላክ በደሉ፤ እግዚአብሔርም ከፊታቸው ባጠፋቸው በምድሩ አሕዛብ አማልክት አመነዘሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ለአባቶቻቸው አምላክ አልታመኑም፤ እግዚአብሔር ከፊታቸው ያጠፋቸውን የምድሪቱን አሕዛብ አማልክት በማምለክ አመነዘሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአባቶቻቸውንም አምላክ በደሉ፥ እግዚአብሔርም ከፊታቸው ባጠፋቸው በምድሩ አሕዛብ አማልክት አመነዘሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ለቀድሞ አባቶቹ አምላክ ታማኝ ሆኖ አልተገኘም፤ እንዲያውም እግዚአብሔርን ትቶ ከምድሪቱ ላይ ላስወገደለት ሕዝብ አማልክት ሰገደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአባቶቻቸውንም አምላክ በደሉ፤ እግዚአብሔርም ከፊታቸው ባጠፋቸው በምድሩ አሕዛብ አማልክት አመነዘሩ። |
በዘመኑም የአሶር ንጉሥ ፎሐ በምድሪቱ ላይ ወጣ፤ ምናሔምም የፎሐ እጅ ከእርሱ ጋር እንዲሆን አንድ ሺህ መክሊት ብር ሰጠው።
የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፥ ይስዔ፥ ኤሊኤል፥ ዓዝርኤል፥ ኢይርምያ፥ ሆዳይዋ፥ ኢየድኤል፤ እነርሱ ጽኑዓን ኀያላን የታወቁ ሰዎች የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች ነበሩ።
እስራኤልም ሁሉ ስለ ኀጢአታቸው ወደ ባቢሎን ከተማረኩ በኋላ፥ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
በዚያች ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ፥ እነርሱ አምላኮቻቸውን ተከትለው በአመነዘሩና በሠዉላቸው ጊዜ እንዳይጠሩህ፥ ከመሥዋዕታቸውም እንዳትበላ፥
ወደ ሆሴዕ የመጣ የእግዚአብሔር የቃሉ መጀመሪያ ይህ ነው፤ እግዚአብሔር ሆሴዕን፥ “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታመነዝራለችና ሂድ፤ ዘማዊቱን ሴትና የዘማዊቱን ልጆች ለአንተ ውሰድ” አለው።
እስራኤል ሆይ! ከአምላክህ ርቀህ አመንዝረሃልና እንደ አሕዛብ ደስ አይበልህ፤ ሐሴትንም አታድርግ፤ ከእህሉና ከወይኑ አውድማ ሁሉ ይልቅ የግልሙትና ዋጋን ወድደሃል።
ከግብፅ ምድርም ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፤ ሌሎችንም በዙሪያቸው ያሉ የአሕዛብን አማልክት ተከተሉ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔርንም አስቈጡት።
ሌሎች አማልክትን ተከትለው አመነዘሩ፤ ሰገዱላቸውም እንጂ፥ መሳፍንቶቻቸውን አልሰሙም፤ እግዚአብሔርንም አስቈጡት፤ የእግዚአብሔርንም ቃል እንዳይሰሙ አባቶቻቸው ይሄዱባት የነበረችውን መንገድ ፈጥነው ተዉአት፤ እንዲሁም አላደረጉም።
እንዲህም ሆነ፤ ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመለሱ፤ በዓሊምንም ተከትለው አመነዘሩ፤ በዓሊምም አምላክ ይሆናቸው ዘንድ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገቡ።