በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና በእርሱም ታምነዋልና አዳናቸው፤ በላያቸውም በረቱባቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተሰጡ።
1 ዜና መዋዕል 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከከብቶቻቸውም አምሳ ሺህ ግመሎች፥ ሁለት መቶ አምሳ ሺህም በጎች፥ ሁለት ሺህም አህዮች፥ ከሰዎችም መቶ ሺህ ማረኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአጋራውያንንም እንስሳት ማረኩ፤ እነዚህም ዐምሳ ሺሕ ግመሎች፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሺሕ በጎችና ሁለት ሺሕ አህዮች ነበሩ። እንዲሁም አንድ መቶ ሺሕ ሰው ማረኩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእንስሶቻቸውም ኀምሳ ሺህ ግመሎች፥ ሁለት መቶ ኀምሳ ሺህም በጎች፥ ሁለት ሺህም አህዮች፥ ከሰዎችም መቶ ሺህ ማረኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጠላትም እጅ ኀምሳ ሺህ ግመሎችን፥ ሁለት መቶ ኀምሳ ሺህ በጎችንና ሁለት ሺህ አህዮችን ማረኩ፤ እንዲሁም አንድ መቶ ሺህ ሰዎችን ምርኮኛ አድርገው ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከብቶቻቸውም አምሳ ሺህ ግመሎች፥ ሁለት መቶ አምሳ ሺህም በጎች፥ ሁለት ሺህም አህዮች፥ ከሰዎችም መቶ ሺህ ማረኩ። |
በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና በእርሱም ታምነዋልና አዳናቸው፤ በላያቸውም በረቱባቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተሰጡ።
ድንኳናቸውንና በጎቻቸውን ይወስዳሉ፤ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ፥ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው ይወስዳሉ፤ በዙሪያቸውም ሁሉ ጥፋትን ጥሩባቸው።
ቀረፋም፥ ቅመምም፥ የሚቃጠልም ሽቱ፥ ቅባትም፥ ዕጣንም፥ የወይን ጠጅም፥ ዘይትም፥ የተሰለቀ ዱቄትም፥ ስንዴም፥ ከብትም፥ በግም፥ ፈረስም፥ ሰረገላም፥ ባሪያዎችም፥ የሰዎችም ነፍሳት ነው።