1 ዜና መዋዕል 4:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ በነጣዔምና በጋዲራ ከንጉሡ ጋር የሚቀመጡ ሸክላ ሠራተኞች ነበሩ። እነርሱም በመንግሥቱ ጸንተው በዚያ ይኖሩ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹ በነጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠሪዎች ነበሩ፤ በዚያም በመቀመጥ ለንጉሡ ሸክላ ይሠሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ በነጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠራተኞች ነበሩ። በዚያ የንጉሡን ሥራ ለመሥራት በእርሱ ዘንድ ይቀመጡ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም የቤተ መንግሥት ሸክላ ሠራተኞች ሆነው ነጣዒምና ገዴራ ተብለው በሚጠሩ ከተሞች ይኖሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ዝና ከቀድሞ ጀምሮ ነበረ። እነዚህ በነጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠራተኞች ነበሩ። በዚያ በንጉሡ ዘንድ ስለ ሥራው ይቀመጡ ነበር። |