ሚስቱ አይሂዳም የጌዶርን አባት ያሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህ ሞሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።
1 ዜና መዋዕል 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሆድያ ሚስት የነሐም እኅት ልጆች የገርሜው የቅዔላ አባትና ማዕካታዊው ኤሲትሞዓ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ወንዶች ልጆች፤ የገርሚው የቅዒላ አባት፣ ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ልጆች የገርሚው የቅዒላ አባትና ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆድያም የናሐምን እኅት አገባ፤ የእነርሱም ዘሮች በቀዒላ ከተማ ይኖሩ ለነበሩት ለጋርሚ ጐሣዎችና በኤሽተሞዓ ከተማ ይኖሩ ለነበሩት ለማዕካት ጐሣዎች አባቶች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ልጆች የገርሚው የቅዒላ አባትና ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ ነበሩ። |
ሚስቱ አይሂዳም የጌዶርን አባት ያሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህ ሞሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።