1 ዜና መዋዕል 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢኮንያንም ልጆች አሤር፥ ሰላትያል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምርኮኛው የኢኮንያን ዘሮች፤ ልጁ ሰላትያል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምርኮኛውም የኢኮንያን ልጆች፤ ልጁ ሰላትያል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ምርኮኛ የነበረው የኢኮንያን ልጆች ሰላትያል፥ ማልኪራም፥ ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ፥ ሆሻማዕና ነዳብያ ተብለው የሚጠሩ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምርኮኛውም የኢኮንያን ልጆች ሰላትያል፥ |
የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ፥ ወንድሞቹም ካህናቱ፥ የሰላትያልም ልጅ ዘሩባቤል፥ ወንድሞቹም ተነሥተው በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡበት ዘንድ የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ።
በኢየሩሳሌምም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛውም ወር የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል፥ የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ወንድሞቻቸው ካህናትና ሌዋውያን፥ ከምርኮ ወደ ኢየሩሳሌምም የተመለሱት ሁሉ ጀመሩ፤ ሌዋውያንንም ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ እንዲያሠሩት ሾሙአቸው።
በዚያን ጊዜም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ ተነሥተው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ፤ የሚያግዙአቸውም የእግዚአብሔር ነቢያት ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በዘመኑ አይከናወንምና፥ ከዘሩም በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ አይነሣምና፥ እንግዲህ ወዲህም ለይሁዳ ገዢ አይሾምምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠሪው” አለ።