1 ዜና መዋዕል 27:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሦስተኛው ወር ሦስተኛው የጭፍራ አለቃ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሽህ ጭፍራ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስተኛውም ወር፣ የሦስተኛው ክፍለ ጦር የበላይ አዛዥ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ ዋናው እርሱ ሲሆን፣ በሥሩ ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሦስተኛው ወር ሦስተኛው የሠራዊቱ አለቃ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ በእነርሱም ክፍል ውስጥ ሀያ አራት ሺህ አባላት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሦስተኛው ወር ሦስተኛው የጭፍራ አለቃ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። |
ንጉሡም በእርሱ ፋንታ የዮዳሄን ልጅ በንያስን የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመ፤ መንግሥቱም በኢየሩሳሌም ጸናች። በአብያታርም ፋንታ ካህኑን ሳዶቅን ሾመ።
በሁለተኛውም ወር ክፍል ላይ የኤቲ ልጅ ዶድያ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሚኮሎት አለቃ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።