1 ዜና መዋዕል 27:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአኪጦፌልም ቀጥሎ የበናያስ ልጅ ዮዳሔና አብያታር ነበሩ፤ ኢዮአብም የንጉሡ ሠራዊት አለቃ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር በአኪጦፌል እግር ተተኩ። ኢዮአብም የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአኪጦፌልም ቀጥሎ የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር ነበሩ፤ ኢዮአብም የንጉሡ ሠራዊት አለቃ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አኪጦፌል ከሞተ በኋላም አብያታርና የበናያ ልጅ ይሆያዳዕ የንጉሡ አማካሪዎች ሆኑ፤ ኢዮአብ ደግሞ የንጉሡ ሠራዊት አዛዥ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአኪጦፌልም ቀጥሎ የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር ነበሩ፤ ኢዮአብያም የንጉሡ ሠራዊት አለቃ ነበረ። |
ሴራውም ከሶርህያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር ነበረ፤ እነርሱም አዶንያስን ተከትለው ይረዱት ነበር።
ዳዊትም ኢያቡሳውያንን አስቀድሞ የሚመታ ሰው አለቃና መኰንን ይሆናል አለ። የሶርህያም ልጅ ኢዮአብ አስቀድሞ ወጣና ወጋቸው፥ አለቃም ሆነ።
በሦስተኛው ወር ሦስተኛው የጭፍራ አለቃ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሽህ ጭፍራ ነበረ።