ከዚህም በኋላ እንደ ገና በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ሆነ፤ ያን ጊዜም አስጣጦታዊው ሴቤኮይ ከራፋይም ወገን የሆነውን ሳፍን ገደለው።
1 ዜና መዋዕል 27:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስምንተኛው ወር ስምንተኛው አለቃ ከዛራውያን የነበረው ኩሳታዊው ሲቦካይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በስምንተኛው ወር፣ ስምንተኛው የበላይ አዛዥ ከካዛራውያን ወገን የሆነው ኩሳታዊው ሴቦካይ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለስምንተኛው ወር ስምንተኛው አለቃ ከዛራውያን የነበረው ኩሳታዊው ሲቦካይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ውስጥ ሀያ አራት ሺህ አባላት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለስምንተኛው ወር ስምንተኛው አለቃ ከዛራውያን የነበረው ኩሳታዊው ሲቦካይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ። |
ከዚህም በኋላ እንደ ገና በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ሆነ፤ ያን ጊዜም አስጣጦታዊው ሴቤኮይ ከራፋይም ወገን የሆነውን ሳፍን ገደለው።
ከዚህም በኋላ በጋዜር ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት እንደ ገና ሆነ፤ ያንጊዜም ኡሳታዊው ሴቦቃይ ከኀያላን ወገን የነበረውን ሲፋይን ገድሎ ጣለው።
በሰባተኛውም ወር ሰባተኛው አለቃ ከኤፍሬም ልጆች የሆነ ፍሎሳዊው ከሊስ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
በዘጠነኛው ወር ዘጠነኛው አለቃ ከብንያማውያን የነበረው ዓናቶታዊው አቢዔዜር ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።