1 ዜና መዋዕል 24:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ከአልዓዛር ልጆች ሳዶቅን፥ ከኢታምርም ልጆች አቤሜሌክን እንደ ቍጥራቸው፥ እንደ አገልግሎታቸውና እንደ እየአባቶቻቸው ቤቶች ከፍሎ መደባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም የአልዓዛር ዘር የሆነው ሳዶቅና የኢታምር ዘር የሆነው አቢሜሌክ እየረዱት እንደየአገልግሎታቸው ሥርዐት እየለየ መደባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ከአልዓዛር ልጆች ከሳዶቅ ጋር፥ ከኢታምርም ልጆች ከአቢሜሌክ ጋር ሆኖ እንደ አገልግሎታቸው ሥርዓርት ከፍሎ መደባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዳዊት የአሮንን ዘሮች እንደየሥራ ምድባቸው በቡድን በቡድን ከፈላቸው፤ ይህንንም ያደረገው የአልዓዛር ዘር በሆነው በሳዶቅና የኢታማር ዘር በሆነው በአቤሜሌክ ረዳትነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ከአልዓዛር ልጆች ከሳዶቅ ጋር፥ ከኢታምርም ልጆች ከአቢሜሌክ ጋር ሆኖ እንደ አገልግሎታቸው ሥርዐርት ከፍሎ መደባቸው። |
ንጉሡም በእርሱ ፋንታ የዮዳሄን ልጅ በንያስን የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመ፤ መንግሥቱም በኢየሩሳሌም ጸናች። በአብያታርም ፋንታ ካህኑን ሳዶቅን ሾመ።
ዳዊትም ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን፥ ሌዋውያንንም፥ ኡርኤልን፥ ዓሣያን፥ ኢዮኤልን፥ ሰማያን፥ ኤሊኤልን፥ አሚናዳብንም ጠርቶ፦
ካህኑን ሳዶቅንና ካህናቱን ወንድሞቹን በገባዖን በኮረብታው መስገጃ ባለው በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት አቆማቸው፥
እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላላቆች እንደ ታናናሽ ወንድሞቻቸው፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምር ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ዐሥራ ስድስት አለቆች፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ።
ከሌዋውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሓፊው ሳምያስ በንጉሡና በአለቆቹ ፊት ፥ በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቤሜሌክ ፊት ፥ በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት ጻፋቸው፤ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር፥ አንዱንም ለኢታምር ጻፈ።
የእግዚአብሔርም ሰው ዳዊት እንዲህ አዝዞ ነበርና ካህናቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥርዐት በየአገልግሎታቸው ሰሞን ከፈላቸው፤ ሌዋውያንም እንደ ሥርዐታቸው ያመሰግኑ ዘንድ፥ በካህናቱም ፊት ያገለግሉ ዘንድ በየሰሞናቸው ከፈላቸው፤ በረኞቹንም ደግሞ በየበሩ ሁሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው።
ዳዊትም ወደ ካህኑ ወደ አቤሜሌክ ወደ ኖብ መጣ፤ አቤሜሌክም እርሱን በተገናኘው ጊዜ ደነገጠ፥ “ስለምን አንተ ብቻህን ነህ? ከአንተስ ጋር ስለምን ማንም የለም?” አለው።