1 ዜና መዋዕል 2:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኦርም ኡሪን ወለደ፥ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሑር ኡሪን ወለደ፤ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሆርም ኡሪን ወለደ፥ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሑርም ኡሪ የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ኡሪም ባጽልኤል ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሆርም ኡሪን ወለደ፤ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ። |
ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወደ አገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኬር ልጅ ገባ፤ ሴጉብንም ወለደችለት።
የሆርም ልጅ የኡሪ ልጅ ባስልኤል የሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ነበረ፤ ሰሎሞንና የእስራኤልም ጉባኤ የእግዚአብሔርን ታቦት ይፈልጓት ነበር።
ባስልኤልም ከማይነቅዝ ዕንጨት ታቦትን ሠራ፤ ርዝመቷ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርድዋ አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቷም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ።