አቤሴሎምም በሠራዊቱ ላይ በኢዮአብ ስፍራ አሜሳይን ሾመ፤ አሜሳይም የኢዮአብን እናት የሶርህያን እኅት የነዓሶንን ልጅ አቢግያን የአገባው የኢይዝራኤላዊው የዮቶር ልጅ ነበር።
1 ዜና መዋዕል 2:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቢግያም አሜሳይን ወለደች፤ የአሜሳይም አባት እስማኤላዊው ይትኤር ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቢግያ አሜሳይን ወለደች፤ አባቱም ዬቴር የተባለ እስማኤላዊ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቢግያም አሜሳይን ወለደች፤ የአሜሳይም አባት እስማኤላዊው ዬቴር ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላይቱ የእሴይ ሴት ልጅ አቢጌል የእስማኤል ዘር የሆነውን ዬቴርን አግብታ ዐማሣ ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቢግያም አሜሳይን ወለደች፤ የአሜሳይም አባት እስማኤላዊው ዬቴር ነበር። |
አቤሴሎምም በሠራዊቱ ላይ በኢዮአብ ስፍራ አሜሳይን ሾመ፤ አሜሳይም የኢዮአብን እናት የሶርህያን እኅት የነዓሶንን ልጅ አቢግያን የአገባው የኢይዝራኤላዊው የዮቶር ልጅ ነበር።
ለአሚሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቍራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።”
አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ከእርሱ የሚሻሉትን ሁለቱን ጻድቃን ሰዎች፥ የእስራኤልን ሠራዊት አለቃ የኔርን ልጅ አበኔርን፥ የይሁዳንም ሠራዊት አለቃ የኢያቴርን ልጅ አሜሳይን በሰይፍ ገድሎአልና እግዚአብሔር የዐመፅ ደሙን በራሱ ላይ መለሰ።
አንተም ደግሞ የሶርህያ ልጅ ኢዮአብ፥ ሁለቱን የእስራኤል ሠራዊት አለቆች የኔር ልጅ አበኔርን የኢያቴርንም ልጅ አሜሳይን ገድሎ፥ በእኔ ላይ ያደረገውን ታውቃለህ፤ የጦርነትንም ደም በሰላም አፈሰሰ፤ በወገቡም ባለው ድግና በእግሩም ባለው ጫማ ንጹሕ ደም አኖረ።
መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ መጣ፤ እርሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ ውጣ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊትም ተቀበላቸው፤ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።