የአሞንም ልጆች ወጥተው በበሩ መግቢያ ፊት ለፊት ይዋጉ ጀመሩ፤ የሱባና የሮዖብ ሶርያውያን፥ የአስጦብና የአማሌቅም ሰዎች ለብቻቸው በሰፊ ሜዳ ላይ ነበሩ።
1 ዜና መዋዕል 19:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሞንም ልጆች ወጥተው በከተማዪቱ በር አጠገብ ተሰለፉ፤ የመጡትም ነገሥታት ለብቻቸው በሜዳው ላይ ሰፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞናውያንም መጥተው ወደ ከተማቸው በሚያስገባው በር ላይ ለጦርነት ተሰለፉ፤ የመጡት ነገሥታት ደግሞ ብቻቸውን በሜዳው ላይ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሞንም ልጆች ወጥተው በከተማይቱ በር አጠገብ ለውግያ ተሰለፉ፤ የመጡትም ነገሥታት ለብቻቸው በሜዳው ላይ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሞናውያንም ተሰልፈው መጥተው የእነርሱ ዋና ከተማ በሆነችው በራባ መግቢያ በር አጠገብ ስፍራቸውን ያዙ፤ እነርሱን ሊረዱ የመጡ ነገሥታትም ገላጣማ በሆነው ገጠር ስፍራቸውን ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሞንም ልጆች ወጥተው በከተማይቱ በር አጠገብ ተሰለፉ፤ የመጡትም ነገሥታት ለብቻቸው በሜዳው ላይ ነበሩ። |
የአሞንም ልጆች ወጥተው በበሩ መግቢያ ፊት ለፊት ይዋጉ ጀመሩ፤ የሱባና የሮዖብ ሶርያውያን፥ የአስጦብና የአማሌቅም ሰዎች ለብቻቸው በሰፊ ሜዳ ላይ ነበሩ።
ንጉሡም፥ “በፊታችሁ መልካም የሚመስላችሁን አደርጋለሁ” አላቸው። ንጉሡም በበሩ አጠገብ ቆመ፤ ሕዝቡም ሁሉ መቶ በመቶ፥ ሺህ በሺህ እየሆኑ ወጡ።
ኢዮአብም በፊቱና በኋላው ሰልፍ እንደ ከበበው ባየ ጊዜ ከእስራኤል ጐልማሶችን መረጠ፤ እነርሱም ከሶርያውያን ጋር ተዋጉ።
አብያም የተመረጡትን አራት መቶ ሺህ ኀያላን ሰልፈኞች ይዞ ወደ ሰልፍ ወጣ፤ ኢዮርብዓምም የተመረጡትን ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ይዞ በእርሱ ላይ ተሰለፈ።
ቀስትና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተምማል፤ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ እንደ እሳት በአንቺ ላይ ይሰለፋሉ።
ድምፃቸውም በተራራ ላይ እንደ አሉ ሠረገሎች ድምፅ፥ ገለባውንም እንደሚበላ እንደ እሳት ነበልባል ድምፅ ነው፤ ለሰልፍም እንደ ተዘጋጀ እንደ ብዙና ብርቱ ሠራዊት ያኰበኵባሉ።