1 ዜና መዋዕል 19:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የአሞን ልጆች ንጉሥ ናዖስ ሞተ፤ ልጁም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ ሞተ፤ ልጁም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ ሞተ፥ ልጁም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጥቂት ጊዜ በኋላ የዐሞን ንጉሥ ናዖስ ሞተ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ሐኑን ነገሠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ የአሞን ልጆች ንጉሥ ናዖስ ሞተ፤ ልጁም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
ዳዊትም፥ “አባቱ ስላደረገልኝ ወረታ እኔ ለናዖስ ልጅ ለሐናን ቸርነት አደርጋለሁ” አለ። ዳዊትም አባቱ ስለ ሞተ ሊያጽናናው መልእክተኞችን ላከ፤ የዳዊትም አገልጋዮች ሊያጽናኑት ወደ ሐናን ወደ አሞን ልጆች ምድር መጡ።
የአሞንም ልጆች ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ንጉሣችሁ ሳለ፦ እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን አላችሁኝ።