ዳዊትም በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውን ግዛቱን ለማጽናት በሄደ ጊዜ ሔማታዊውን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን መታ።
1 ዜና መዋዕል 18:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሶርያውያንም የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ለመርዳት ከደማስቆ በመጡ ጊዜ፣ ዳዊት ሃያ ሁለት ሺሕ ሰው ገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውያን ሀያ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደማስቆ ያሉ ሶርያውያን የጾባን ንጉሥ ሀዳድዔዜርን ለመርዳት ሠራዊት በላኩ ጊዜ ዳዊት በእነርሱም ላይ አደጋ ጥሎ ኻያ ሁለት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደለ። |
ዳዊትም በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውን ግዛቱን ለማጽናት በሄደ ጊዜ ሔማታዊውን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን መታ።
ዳዊትም ከእርሱ አንድ ሺህ ሰረገሎች፥ ሰባት ሺህም ፈረሰኞች፥ ሃያ ሺህም እግረኞች ወሰደ፤ ዳዊትም ለመቶ ሰረገሎች የሚሆኑትን ብቻ አስቀርቶ የሰረገሎቹን ፈረሶች ቋንጃ ቈረጠ።
ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮችን አኖረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ያድነው ነበር።
የአሞንም ልጆች የዳዊት ሰዎች እንዳፈሩ ባዩ ጊዜ ሐናን የአሞን ልጆች ንጉሥ ከሶርያ መስጴጦምያ፥ ከሶርያ ሞዓካ፥ ከሱባም ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን ይቀጥሩ ዘንድ አንድ ሺህ መክሊት ብር ላከ።
ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፤ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከቢዖርም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።