La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 18:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቶዑም ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ጋር ሁል​ጊዜ ይዋጋ ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ወግቶ ስለ መታው ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይ​ቀ​ውና ይመ​ር​ቀው ዘንድ ልጁን አዶ​ራ​ምን ወደ ዳዊት ላከው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የወ​ር​ቅና የብር፥ የና​ስም ዕቃ ነበረ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እጅ እንዲነሣውና ደስታውንም እንዲገልጥለት ልጁን አዶራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ ቶዑ ከአድርአዛር ጋራ ብዙ ጊዜ ጦርነት ገጥሞ ነበር። አዶራምም ከወርቅ፣ ከብርና ከናስ የተሠሩ ልዩ ልዩ ዕቃዎች አመጣለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ወግቶ ድል ስለ አደረገው ደኅንነቱን እንዲጠይቀውና እንዲመርቀው ልጁን አዶራምን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የወርቅና የብር የናስም ዕቃ ይዞ መጣ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቶዒ ከሀዳድዔዜር ጋር ብዙ ጊዜ ጦርነት አድርጎ ስለ ነበር፥ ንጉሥ ዳዊትን እጅ እንዲነሣና በሀዳድዔዜር ላይ ስለ ተቀዳጀው ድል ደስታውን እንዲገልጥለት ልጁን ዮራምን ወደ ዳዊት ላከ። ዮራምም ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ የተሠሩ ዕቃዎችን ገጸ በረከት አድርጎ ለዳዊት አመጣለት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁል ጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ወግቶ ስለ መታው ደኅንነቱን ይጠይቅ ዘንድ ይመርቀው ዘንድ ልጁን አዶራምን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የወርቅና የብር የናስም ዕቃ ይዞ መጣ።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 18:10
6 Referencias Cruzadas  

ታይም የአ​ድ​ር​አ​ዛር ጠላት ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ስለ ተዋ​ጋ​ውና ስለ ገደ​ለው፥ ታይ ልጁን ኢያ​ዱ​ራን ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይቅ ዘንድ፥ ይመ​ር​ቀ​ውም ዘንድ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እር​ሱም የብ​ርና የወ​ርቅ የና​ስም ዕቃ ይዞ መጣ፤


ንጉ​ሡም ዳዊት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ከኤ​ዶ​ምና ከሞ​ዓብ፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ከአ​ማ​ሌ​ቅም ከማ​ረ​ከው ብርና ወርቅ ጋር እነ​ዚ​ህን ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ።


የኤ​ማ​ትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን፥ ጭፍ​ራ​ው​ንም ሁሉ እንደ መታ ሰማ።


የሳ​ባም ንግ​ሥት የሰ​ሎ​ሞ​ንን ዝና በሰ​ማች ጊዜ በግ​መ​ሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ አስ​ጭና ከታ​ላቅ ጓዝ ጋር ሰሎ​ሞ​ንን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ን​ቆ​ቅ​ልሽ ትፈ​ት​ነው ዘንድ መጣች፤ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም በገ​ባች ጊዜ በል​ብዋ ያለ​ውን ሁሉ አጫ​ወ​ተ​ችው።


በዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የባ​ል​ዳን ልጅ መሮ​ዳክ ባል​ዳን ሕዝ​ቅ​ያስ ታምሞ እንደ ተፈ​ወሰ ሰምቶ ነበ​ርና ደብ​ዳ​ቤና እጅ መን​ሻን፥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ላከ​ለት።