የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፤ የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።
1 ዜና መዋዕል 17:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክ ሆይ፥ ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፤ ስለ አገልጋይህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ። አቤቱ፥ አምላክ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ ይህ በፊትህ በቂ እንዳልሆነ ቈጥረህ ስለ ወደ ፊቱ የባሪያህ ቤት ተናገርህ። እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ እኔንም ከሰዎች ሁሉ እጅግ የከበረ ሰው አድርገህ ተመለከትኸኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላክ ሆይ! ይህ በፊትህ ጥቂት የሆነ ነገር ነበረ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ! ስለ ባርያህ ቤት ደግሞ ስለ ወደ ፊቱ ሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ያለፈው ሁሉ በፊትህ የማይበቃ ሆኖ ስለ አገልጋይህ ቤት ለሚመጣው ሩቅ ዘመን አሁንም እንደገና እኔን እንደ ትልቅ ባለማዕርግ አድርገህ ተመለከትከኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክ ሆይ! ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ! ስለ ባሪያህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕረግ ሰው ተመለከትኸኝ። |
የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፤ የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።
ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ እኔ በፊትህ እጅግ ታናሽ ስሆን ስለ ባሪያህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህ የሰው ሕግ ነው።
ንጉሡም ዳዊት ገባ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፥ “አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ለዘለዓም የወደድኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው?
እርሱም፥ “የያዕቆብን ነገዶች እንደገና እንድታስነሣ፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ወደ አባቶች ቃል ኪዳን እንድትመልስ ባርያዬ ትሆን ዘንድ ለአንተ እጅግ ታላቅ ነገር ነውና፥ እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኀኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ” ይላል።
በከሃሊነቱ እንደ ረዳን መጠን፥ የምናስበውንና የምንለምነውን ሁሉ ትሠሩ ዘንድ፥ ታበዙም ዘንድ ሊያጸናችሁ ለሚችል፥