ንጉሡ ነቢዩ ናታንን፥ “እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጬአለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ተቀምጣለች” አለው።
1 ዜና መዋዕል 14:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጢሮስም ንጉሥ ኪራም ቤት ይሠሩለት ዘንድ መልእክተኞችን፥ የዝግባ እንጨትንም፥ ጠራቢዎችንም፥ አናጢዎችንም ወደ ዳዊት ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት እንዲሠሩ መልክተኞችን፣ ድንጋይ ጠራቢዎችንና የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችን ከዝግባ ዕንጨት ጋራ ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጢሮስም ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤት እንዲሠሩለት መልእክተኞችን የዝግባ እንጨትንም ጠራቢዎችንም አናጢዎችንም ወደ ዳዊት ላከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጢሮስ ንጉሥ ኪራም መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ፤ ከእነርሱም ጋር ለዳዊት ቤተ መንግሥት የሚሠሩለት የሊባኖስ ዛፍ ግንድ የያዙ አናጢዎችና ግንበኞች ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጢሮስም ንጉሥ ኪራም ቤት ይሠሩለት ዘንድ መልእክተኞችን የዝግባ እንጨትንም ጠራቢዎችንም አናጢዎችንም ወደ ዳዊት ላከ። |
ንጉሡ ነቢዩ ናታንን፥ “እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጬአለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ተቀምጣለች” አለው።
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለአባቱ ለዳዊት በዘመኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎሞን በአባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ አገልጋዮቹን ወደ ሰሎሞን ላከ።
የሰሎሞንና የኪራም አናጢዎች፥ ጌባላውያንም ወቀሩአቸው፤ ለመሠረትም አኖሩአቸው፤ ቤቱንም ለመሥራት እንጨቱንና ድንጋዮቹን ሦስት ዓመት አዘጋጁ።
አሁንም ከወገኔ እንደ ሲዶናውያን እንጨት መቍረጥ የሚያውቅ እንደሌለ ታውቃለህና የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ ይቈርጡልኝ ዘንድ አገልጋዮችህን እዘዝ፤ አገልጋዮቼም ከአገልጋዮችህ ጋር ይሁኑ፤ የአገልጋዮችህንም ዋጋ እንደ ተናገርኸው ሁሉ እሰጥሃለሁ።”
ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል፥ መንግሥቱ እጅግ ከፍ ብሎአልና እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን እንዳዘጋጀው ዳዊት ዐወቀ።
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩ ናታንን፥ “እነሆ፥ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ግን በመጋረጃዎች ውስጥ ተቀምጣለች” አለው።
ዳዊትም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ይሰበስቡ ዘንድ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ለመሥራት የሚወቀሩትን ድንጋዮች ይወቅሩ ዘንድ ጠራቢዎችን አኖረ።
ሰሎሞንም የሚሸከሙትን ሰባ ሺህ፥ ከተራሮችም ድንጋዮችን የሚጠርቡትን ሰማንያ ሺህ፥ በእነርሱም ላይ የተሾሙትን ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች ሰበሰበ።
ሰሎሞንም እንዲህ ሲል ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ላከ፥ “ከአባቴ ከዳዊት ጋር እንዳደረግህ፥ የሚቀመጥበትንም ቤት ይሠራ ዘንድ የዝግባ እንጨት እንደ ላክህለት፥ እንዲሁ ለእኔ አድርግ።
ለጠራቢዎችና ለአናጢዎችም ብር ሰጡ፤ የፋርስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀደላቸው የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ በባሕር ወደ ኢዮጴ ያመጡ ዘንድ ለሲዶናና ለጢሮስ ሰዎች መብልና መጠጥ፥ ዘይትም ሰጡ።