መዘምራኑ በሚዘምሩበትና መለከተኞቹም በሚነፉበት ጊዜም መላው ጉባኤ አጐንብሰው ሰገዱ፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት እስኪጠናቀቅ ድረስም ይህ ሁሉ ቀጠለ።
መዝሙር 96:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተቀደሰ ውበት ለእግዚአብሔር ስገዱ፤ ምድር ሁሉ፤ በፊቱ ተንቀጥቀጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቅድስናው ስፍራ ለጌታ ስገዱ፥ ምድር ሁሉ በፊቱ ትናወጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግርማ በተመላ ቅድስናው ለእግዚአብሔር ስገዱ! የምድር ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጡ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ፥ እግዚአብሔር፥ በምድር ላይ ሁሉ ብቻህን ልዑል ነህና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃልና። |
መዘምራኑ በሚዘምሩበትና መለከተኞቹም በሚነፉበት ጊዜም መላው ጉባኤ አጐንብሰው ሰገዱ፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት እስኪጠናቀቅ ድረስም ይህ ሁሉ ቀጠለ።
ንጉሥ ሕዝቅያስና ሹማምቱ፣ ሌዋውያኑ በዳዊትና በባለራእዩ በአሳፍ ቃል እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ አዘዙ። እነርሱም ውዳሴውን በደስታ ዘመሩ፤ ራሳቸውንም አጐንብሰው ሰገዱ።
ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ ከንጋት ማሕፀን፣ በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣ የጕልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ።
በውብ ዕንቋቸው ታብየዋል፤ ይህንም አስጸያፊ የጣዖት ምስሎቻቸውንና ርኩስ ቅርጻ ቅርጾችን ለመሥራት ተጠቅመውበታል። ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ወደ ርኩሰት እለውጥባቸዋለሁ።