መዝሙር 92:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው! ሐሳብህስ ምን ያህል ጥልቅ ነው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና፥ በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው! ሐሳብህስ እንዴት ጥልቅ ነው! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምስክርህ እጅግ የታመነ ነው፤ አቤቱ፥ እስከ ረዥም ዘመን ድረስ ለቤትህ ምስጋና ይገባል። |
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ ያደረግኸው ድንቅ ነገር ብዙ ነው፤ ለእኛ ያቀድኸውን፣ ሊዘረዝርልህ የሚችል ማንም የለም፤ ላውራው ልናገረው ብል፣ ስፍር ቍጥር አይኖረውም።
የእግዚአብሔር ባሪያ የሆነውን የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፤ “ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ ሆይ፤ ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው። የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ፤ መንገድህ ጽድቅና እውነት ነው።