“ ‘ይህን ቀድሞ እንደ ወሰንሁት፣ አልሰማህምን? ጥንትም እንዳቀድሁት፣ አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ ይህም የተመሸጉትን ከተሞች፣ አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።
መዝሙር 9:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶች ለዘላለም ጠፉ፤ ከተሞቻቸውንም ገለባበጥሃቸው፤ መታሰቢያቸውም ተደምስሷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብን ገሠጽህ፥ ክፉዎችንም አጠፋህ፥ ስማቸውንም ለዘለዓለም ደመሰስህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቻችን ለዘለዓለም ጠፍተዋል፤ ከተሞቻቸውንም ደምስሰሃል፤ መታሰቢያቸውም ጠፍቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶች በጦር ለዘለዓለም ጠፉ፥ ከተሞቻቸውንም አፈረስህ፥ ዝክራቸውንም በአንድነት ታጠፋለህ። |
“ ‘ይህን ቀድሞ እንደ ወሰንሁት፣ አልሰማህምን? ጥንትም እንዳቀድሁት፣ አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ ይህም የተመሸጉትን ከተሞች፣ አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።
ሙሴም ለሕዝቡ መለሰላቸው፤ “አትሸበሩ፣ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር ዛሬ የሚያደርግላችሁን መታደግ ታያላችሁ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብጻውያንን ዳግም አታዩአቸውም።
አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህ እስከሚያልፉ ድረስ፣ የተቤዠሃቸው ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፣ ድንጋጤና ሽብር በእነርሱ ላይ ይመጣል፤ በክንድህ ብርታት፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።
እነርሱ ሞተዋል፤ ከእንግዲህ በሕይወት አይኖሩም፤ መንፈሳቸው ተነሥቶ አይመጣም። አንተ ቀጣሃቸው፤ አጠፋሃቸው፤ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ደመሰስህ።
“ይህን ቀድሞ እንደ ወሰንሁት፣ አልሰማህምን? ጥንትም እንዳቀድሁት አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ ይህም የተመሸጉትን ከተሞች አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።
“አንቺ ምድርን ሁሉ ያጠፋሽ፣ አጥፊ ተራራ ሆይ፤ እኔ በአንቺ ላይ ነኝ፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ ከገመገም ቍልቍል አንከባልልሻለሁ፤ የተቃጠለም ተራራ አደርግሻለሁ።
ጠላቴም ታያለች፤ ኀፍረትንም ትከናነባለች፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ያለችኝን፣ ዐይኖቼ ውድቀቷን ያያሉ፤ አሁንም እንኳ፣ እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።
በሦስተኛው ቀን ዳዊትና ሰዎቹ ጺቅላግ ደረሱ፤ በዚህ ጊዜ አማሌቃውያን ደቡቡን አገርና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ ጺቅላግንም ወግተው አቃጥለው ነበር።
በሸለቆው ማዶና ከዮርዳኖስ ባሻገር ያሉ እስራኤላውያን፣ የእስራኤል ሰራዊት መሸሹን፣ ሳኦልና ልጆቹም መሞታቸውን ሲያዩ፣ ከተሞቻቸውን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።