መለከት ነፊዎችና ዘማሪዎችም በአንድነት አንድ ድምፅ ሆነው ለእግዚአብሔር ውዳሴና ምስጋና አቀረቡ፤ በመለከት፣ በጸናጽልና በሌሎች መሣሪያዎች ታጅበውም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እግዚአብሔርን እያወደሱ፣ “እርሱ ቸር ነው፣ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” እያሉ ዘመሩ። ከዚያም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በደመና ተሞላ።
መዝሙር 81:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዝማሬውን ጀምሩ፤ ከበሮውን ምቱ፤ በበገናና በመሰንቆ ጥዑም ዜማ አሰሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለኃይላችን ለእግዚአብሔር በደስታ ዘምሩ፥ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መዝሙር ለመዘመር ተነሡ፤ ከበሮም ምቱ፤ በበገናና በመሰንቆ ደስ የሚያሰኝ ዜማ አሰሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ መቼ ዐመፃን ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼስ ለኀጢአተኞች ፊት ታደላላችሁ? |
መለከት ነፊዎችና ዘማሪዎችም በአንድነት አንድ ድምፅ ሆነው ለእግዚአብሔር ውዳሴና ምስጋና አቀረቡ፤ በመለከት፣ በጸናጽልና በሌሎች መሣሪያዎች ታጅበውም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እግዚአብሔርን እያወደሱ፣ “እርሱ ቸር ነው፣ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” እያሉ ዘመሩ። ከዚያም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በደመና ተሞላ።
የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ በጥበብ ሁሉ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በማሕሌት፣ በመንፈሳዊም ቅኔ በማመስገን በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።