Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 81:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 መዝሙር ለመዘመር ተነሡ፤ ከበሮም ምቱ፤ በበገናና በመሰንቆ ደስ የሚያሰኝ ዜማ አሰሙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ዝማሬውን ጀምሩ፤ ከበሮውን ምቱ፤ በበገናና በመሰንቆ ጥዑም ዜማ አሰሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ለኃይላችን ለእግዚአብሔር በደስታ ዘምሩ፥ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እስከ መቼ ዐመ​ፃን ትፈ​ር​ዳ​ላ​ችሁ? እስከ መቼስ ለኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ፊት ታደ​ላ​ላ​ችሁ?

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 81:2
11 Referencias Cruzadas  

ባለ አውታር በሆኑት የሙዚቃ መሣሪያዎችና በበገና ቅኝት አንተን ማመስገን እንዴት መልካም ነው?


ከዚያም በኋላ መዝሙር ዘምረው ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ወጡ።


የአሮን እኅት ነቢይቱ ማርያም ከበሮዋን አነሣች፤ ሌሎችም ሴቶች ከበሮዎቻቸውን እየመቱና እየጨፈሩ ይከተሉአት ጀመር፤


ከእናንተ መካከል ችግር የደረሰበት ሰው ቢኖር ይጸልይ፤ ደስ ያለው ሰውም ቢኖር እግዚአብሔርን በማመስገን ይዘምር።


የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።


በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊም ዜማ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ በውዳሴና በመዝሙር በሙሉ ልባችሁ ጌታን አመስግኑ፤


ከእነርሱም ጋር እምቢልታ የሚነፉ አንድ መቶ ኻያ ካህናት ነበሩ፤ እነዚህ መዘምራን ሁሉ በመለከት፥ በጸናጽል፥ በበገናና በሌሎችም የሙዚቃ መሣሪያዎች እየታጀቡ፦ “ቸር ስለ ሆነ፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግኑ” በማለት በአንድ ድምፅ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር። በዚህ ጊዜ በድንገት የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጥ አንጸባራቂ ብርሃን የሞላበት ደመና የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ስለ ሞላው ካህናቱ የአምልኮ አገልግሎታቸውን ሊያከናውኑ አልቻሉም።


እነርሱንም ደግሞ መዕሤያ፥ ሸማዕያ፥ አልዓዛር፥ ዑዚ፥ የሆሐናን፥ ማልኪያ፥ ኤላምና ኤዜር ተከትለዋቸው ይጓዙ ነበር፤ እንደ ቆምንም መዘምራኑ በይዝራሕያ እየተመሩ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ዘመሩ።


አምላክ ሆይ! አንተ ብርታቴ ነህ፤ አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንም ታሳየኛለህ፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios