ደሙም ያላችሁበትን ቤት ለይቶ የሚያሳይ ምልክት ይሆንላችኋል፤ እኔ ደሙን በማይበት ጊዜ እናንተን ዐልፋለሁ፤ ግብጽን ስቀጣ መቅሠፍቱ አይደርስባችሁም።
መዝሙር 74:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምናየው ምልክት የለም፤ ከእንግዲህ የሚነሣ አንድም ነቢይ የለም፤ ይህ እስከ መቼ እንደሚቀጥል የሚያውቅ በእኛ ዘንድ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ አይኖርም፥ ይህም እስከ መቼ እንደሚቆይ የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእንግዲህ ወዲህ ተአምራት አይኖሩም፤ ነቢያትም አይኖሩም፤ ይህ ሁኔታ እስከ መቼ እንደሚቈይ ከእኛ መካከል ማን ያውቃል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን ለዘለዓለም ደስ ይለኛል፥ ለያዕቆብም አምላክ እዘምራለሁ፥ |
ደሙም ያላችሁበትን ቤት ለይቶ የሚያሳይ ምልክት ይሆንላችኋል፤ እኔ ደሙን በማይበት ጊዜ እናንተን ዐልፋለሁ፤ ግብጽን ስቀጣ መቅሠፍቱ አይደርስባችሁም።
በሮቿ ወደ ምድር ሰመጡ፤ የብረት መወርወሪያዎቻቸውን ሰባበረ፤ አጠፋቸውም፤ ንጉሧና መሳፍንቷ በአሕዛብ መካከል ተማርከው ተሰድደዋል፤ ሕጉ ከእንግዲህ አይኖርም፤ ነቢያቷም ከእንግዲህ፣ ከእግዚአብሔር ራእይ አያገኙም።
ጥፋት በጥፋት ላይ፣ ወሬም በወሬ ላይ ይመጣል። ራእይን ከነቢይ ለማግኘት ይጥራሉ፤ የሕግ ትምህርት ከካህኑ፣ ምክርም ከሽማግሌው ዘንድ ይጠፋል።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በምድር ላይ ራብን የምሰድድበት ዘመን ይመጣል፤ ይኸውም የእግዚአብሔርን ቃል የመስማት ራብ እንጂ፣ እንጀራን የመራብ ወይም ውሃን የመጠማት አይደለም።
ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይታይም ነበር።