መዝሙር 7:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤ የሚያድነኝ በሌለበትም ይቦጫጭቁኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካላዳንከኝ ግን እንደ አንበሳ ነጥቀው ማንም ሊታደገኝ ወደማይችል ስፍራ ይወስዱኛል፤ ሰባብረውም ያደቁኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴን እንደ አንበሳ እንዳይነጥቋት፥ የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር። |
ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙላት እንዲሰበክና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳም መንጋጋ አዳነኝ።
የሚኖሩት ከሲዶና በጣም ርቀው ስለ ነበርና ከማንም ጋራ ግንኙነት ስላልነበራቸው የሚታደጋቸው አንድም አልነበረም፤ ከተማዪቱም የምትገኘው በቤትሮዓብ አጠገብ ነበረ። የዳንም ሰዎች ከተማዪቱን እንደ ገና ሠርተው መኖሪያቸው አደረጓት።