አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ በሁለቱ ሰዎች ላይ አደጋ ጥሎ በሰይፍ ገድሏቸዋልና ስላፈሰሰው ደም እግዚአብሔር ይበቀለዋል። የእስራኤል ሰራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔርና የይሁዳ ሰራዊት አዛዥ የዬቴር ልጅ አሜሳይ ሁለቱም ከርሱ የተሻሉና ይበልጥ ትክክለኛ ሰዎች ነበሩ።
መዝሙር 7:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተንኰሉ ወደ ራሱ ይመለሳል፤ ዐመፃውም በገዛ ዐናቱ ላይ ይወርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉድጓድን ማሰ ቈፈረም። በሠራውም ጉድጓድ ይወድቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያመጡት ችግር በራሳቸው ላይ ይደርሳል፤ በክፉ ድርጊታቸውም ዐናታቸው ይፈጠፈጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጉዳቱ በራሱ ይመለሳል፥ ዐመፃውም በአናቱ ላይ ትወርዳለች። |
አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ በሁለቱ ሰዎች ላይ አደጋ ጥሎ በሰይፍ ገድሏቸዋልና ስላፈሰሰው ደም እግዚአብሔር ይበቀለዋል። የእስራኤል ሰራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔርና የይሁዳ ሰራዊት አዛዥ የዬቴር ልጅ አሜሳይ ሁለቱም ከርሱ የተሻሉና ይበልጥ ትክክለኛ ሰዎች ነበሩ።
እንዲህም በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሰውየውን ገደልኸው፤ ደግሞ ርስቱን ልትወስድ?’ ከዚያም እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ቦታ የአንተንም ደም ውሾች እንዲሁ ይልሱታል!’ ”
ሤራው በንጉሡ ዘንድ እንደ ታወቀ ሐማ በአይሁድ ላይ የሸረበው ሤራ በገዛ ራሱ ላይ እንዲጠመጠም፣ እርሱና ወንዶች ልጆቹም በዕንጨት ላይ እንዲሰቀሉ የጽሑፍ ትእዛዝ አስተላለፈ።
እግዚአብሔር አንተንና እስራኤልን ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል፤ አንተና ልጆችህም ነገ ከእኔ ጋራ ትሆናላችሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”