Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 26:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ጕድጓድ የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ ድንጋይ የሚያንከባልልም ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ጉድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፥ ድንጋይንም የሚያንከባልል ይገለበጥበታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ለሌሎች ወጥመድን የሚዘረጉ ሰዎች ራሳቸው ይያዙበታል፤ በሰው ላይ የሚሰዱት የድንጋይ ናዳ እነርሱን መልሶ ይጐዳቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 26:27
11 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሐማን ሰቀሉት፤ ከዚያም የንጉሡ ቍጣ በረደ።


ሤራው በንጉሡ ዘንድ እንደ ታወቀ ሐማ በአይሁድ ላይ የሸረበው ሤራ በገዛ ራሱ ላይ እንዲጠመጠም፣ እርሱና ወንዶች ልጆቹም በዕንጨት ላይ እንዲሰቀሉ የጽሑፍ ትእዛዝ አስተላለፈ።


ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤ በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ።


ለእግሬ ወጥመድን ዘረጉ፤ ነፍሴንም አጐበጧት፤ በመተላለፊያዬ ላይ ጕድጓድ ቈፈሩ፤ ነገር ግን ራሳቸው ገቡበት። ሴላ


አሕዛብ በቈፈሩት ጕድጓድ ገቡ፤ እግራቸውም ራሳቸው በስውር ባስቀመጡት ወጥመድ ተያዘ።


ቅኖችን በክፉ መንገድ የሚመራ፣ በቈፈረው ጕድጓድ ይገባል፤ ንጹሓን ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ።


ክፉውን ሰው የገዛ መጥፎ ሥራው ያጠምደዋል፤ የኀጢአቱም ገመድ ጠፍሮ ይይዘዋል።


ጕድጓድን የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ ቅጥርንም የሚያፈርስ እባብ ይነድፈዋል።


በደለኞች ወዮላቸው! ጥፋት ይመጣባቸዋል! የእጃቸውን ያገኛሉና።


ኢየሩሳሌም ተንገዳግዳለች፤ ይሁዳም ለመውደቅ ተቃርባለች፤ ንግግራቸውም ሆነ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚቃወም፣ የክብሩንም መገኘት የሚያቃልል ነውና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos