መዝሙር 59:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ግን ስለ ኀይልህ እዘምራለሁ፤ በማለዳም ስለ ምሕረትህ እዘምራለሁ፤ አንተ መጠጊያዬ፣ በመከራም ቀን ዐምባዬ ነህና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም መብል ለመፈለግ ይበተኑ፥ ያልጠገቡ እንደሆነም ያላዝኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና ምሽጌ ስለ ሆንክ ስለ ኀያልነትህ ክብርና ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ዘወትር በማለዳ እዘምራለሁ። |
እንዲሁም አሕዛብ እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ ያመሰግኑት ዘንድ ነው፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ “ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ።”
ኢየሱስ በዚህ ምድር በኖረበት ዘመን ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ልመናን ከታላቅ ጩኸትና ከእንባ ጋራ አቀረበ፤ ፍጹም ትሑት ሆኖ በመታዘዙም ጸሎቱ ተሰማለት።
ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያዳነኝ እግዚአብሔር አሁንም ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሳኦልም፣ “ሂድ፤ እግዚአብሔር ካንተ ጋራ ይሁን” አለው።