መዝሙር 57:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሴ በአንበሶች ተከብባለች፤ በሚዘነጣጥሉ አራዊት መካከል ወድቄአለሁ፤ እነዚህም፣ ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ፣ ምላሳቸውም የተሳለ ሰይፍ የሆኑ ሰዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰማይ ልኮ አዳነኝ፥ ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው፥ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነቱን ላከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥርሶቻቸው እንደ ጦሮችና ቀስቶች፥ ምላሶቻቸው እንደ ተሳሉ ሰይፎች በሆኑ፥ ሰውን በሚበሉ አንበሶች መካከል ተደፍቼ ተኝቼአለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍጣቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፥ ጆሮዋም እንደ ደነቈረ እባብ፥ |
ምላስም እንደ እሳት ናት፤ በሰውነት ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ የክፋት ዓለም ናት፤ ሰውነትን ሁሉ ታረክሳለች፤ ደግሞም የፍጥረትን ሩጫ ታቃጥላለች፤ ራሷም በገሃነም ትቃጠላለች።
ሕዝቦችን የሚመታበት ስለታም ሰይፍ ከአፉ ወጣ፤ “በብረት በትርም ይገዛቸዋል።” እርሱም ሁሉን ቻይ የሆነውን የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣ ወይን መጭመቂያ ይረግጣል።
ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቢሜሌክ ትውጣና እናንተን፣ የሴኬምንና የቤት ሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፣ ከሴኬምና ከቤት ሚሎን ገዦች ትውጣና አቢሜሌክን ትብላ።”