Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 52:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አንተ ማታለልን ሥራዬ ብለህ የያዝህ፤ አንደበትህ እንደ ሰላ ምላጭ፣ ጥፋትን ያውጠነጥናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ኤዶማዊው ዶይቅ መጥቶ ለሳኦል፦ ዳዊት ወደ አቢሜሌክ ቤት መጥቷል ብሎ በነገረው ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አንተ ተንኰለኛ ጥፋትህን ታሤራለህ፤ አንደበትህ እንደ ተሳለ ምላጭ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ልግ አስ​ተ​ዋይ እን​ዳለ ያይ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ የሰው ልጆ​ችን ተመ​ለ​ከተ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 52:2
21 Referencias Cruzadas  

ክፉዎችና አታላዮች፣ አፋቸውን ከፍተውብኛልና፤ በውሸተኛ አንደበት ተናግረውብኛል።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሐሰተኛ ከንፈር፣ ከአታላይ ምላስም አድነኝ።


አፍህን ለክፋት አዋልህ፤ አንደበትህም ሽንገላን ጐነጐነ።


ነፍሴ በአንበሶች ተከብባለች፤ በሚዘነጣጥሉ አራዊት መካከል ወድቄአለሁ፤ እነዚህም፣ ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ፣ ምላሳቸውም የተሳለ ሰይፍ የሆኑ ሰዎች ናቸው።


ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት፤ ሰይፍ በከንፈራቸው ላይ አለ፤ “ማን ሊሰማን ይችላል?” ይላሉና።


ግድ የለሽ ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል፤ የጠቢብ አንደበት ግን ፈውስን ያመጣል።


አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤ የሚወድዷትም ፍሬዋን ይበላሉ።


ድኾችን ከምድር፣ ችግረኞችንም ከሰው ዘር መካከል ለማጥፋት፣ ጥርሳቸው ሰይፍ የሆነ፣ መንጋጋቸውም ካራ የሆነ አሉ።


እነርሱም፣ “ሕግ ከካህናት፣ ምክር ከጠቢባን፣ ቃልም ከነቢያት ስለማይታጣ ኑና በኤርምያስ ላይ እንማከር፤ ኑ፤ በአንደበታችን እናጥቃው፣ እርሱ የሚናገረውንም ሁሉ አንስማ” አሉ።


በዚህ ጊዜ የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሸንጎ በሙሉ ኢየሱስን ለማስገደል የሐሰት ማስረጃ ይፈልጉ ነበር፤


ከዐምስት ቀን በኋላ፣ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከአንዳንድ ሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚባል ጠበቃ ጋራ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በጳውሎስም ላይ ያላቸውን ክስ ለአገረ ገዥው አቀረቡ።


“ይህ ሰው፣ በዓለም ባሉት አይሁድ ሁሉ መካከል በሽታ ሆኖ ሁከት የሚያስነሣ፣ ደግሞም የናዝራውያን ወገን ቀንደኛ መሪ ሆኖ አግኝተነዋል።


እንደነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት ለመምሰል ራሳቸውን የሚለዋውጡ፣ ሐሰተኞች ሐዋርያትና አታላዮች ሠራተኞች ናቸው።


ነገር ግን ስውርና አሳፋሪ ነገሮችን ትተናል፤ በማታለል አንመላለስም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ከሐሰት ጋራ አንቀላቅልም፤ ይልቁንም እውነትን በግልጽ እየተናገርን በሰው ሁሉ ኅሊና ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረን ራሳችንን በእግዚአብሔር ፊት እናቀርባለን።


ከዚህ በኋላ ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “አሁን የአምላካችን ማዳን፣ ኀይልና መንግሥት፣ የርሱ ክርስቶስ ሥልጣንም መጥቷል። ቀንና ሌሊት በአምላካችን ፊት ሲከስሳቸው የነበረው፣ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሏልና።


ነገር ግን እዚያ ከነበሩት የሳኦል ሹማምት ጋራ ቆሞ የነበረው ኤዶማዊው ዶይቅ እንዲህ አለ፣ “የእሴይ ልጅ በኖብ ወዳለው ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ አቢሜሌክ ሲመጣ አይቻለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos