መዝሙር 53:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያስፈራ ነገር በሌለበት፣ በዚያ፣ ድንጋጤ ውጧቸዋል፤ እግዚአብሔር የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት በተነ፤ እርሱ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው፣ አንተ አሳፈርሃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉ ግፍ አድራጊዎች ሁሉ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የሕዝቡን ጠላቶች ስለ ሰባበራቸው ከምንጊዜውም ይልቅ በፍርሃት ተጨነቁ፤ እግዚአብሔርም ስለ ጠላቸው ፈጽሞ ያፍራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፋትን ወደ ጠላቶች ይመልሳታል፤ በእውነትህም አጥፋቸው። |
ማደሪያውን እንደ አትክልት ስፍራ ባዶ አደረገ፤ መሰብሰቢያ ስፍራውን አፈረሰ፤ እግዚአብሔር ጽዮንን፣ ዓመት በዓላቶቿንና ሰንበታቷን እንድትረሳ አደረጋት፤ በጽኑ ቍጣው፣ ንጉሡንና ካህኑን እጅግ ናቀ።
“ ‘ከእናንተ በሕይወት የተረፉትን፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ድንጋጤ እሰድድባቸዋለሁ፤ ነፋስ የሚያንቀሳቅሰው የቅጠል ድምፅ ያስበረግጋቸዋል፤ የሚያሳድዳቸውም ሳይኖር ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሮጣሉ፤ ይወድቃሉም።
በሰፈር በዕርሻ ላይና በሕዝብ ሁሉ መካከል ሽብር ሆነ፤ ከተማ ጠባቂዎችና አደጋ ጣዮችም ሁሉ ተንቀጠቀጡ፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ሽብሩም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ነበር።