ይህም የሶርያን ንጉሥ እጅግ ስላበሳጨው፣ የጦር አለቆቹን ጠርቶ፣ “ከመካከላችን ከእስራኤል ንጉሥ ጋራ የተወዳጀ እንዳለ ለምን አትነግሩኝም?” ሲል ጠየቃቸው።
መዝሙር 48:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ነገሥታት ተባብረው መጡ፤ አንድ ላይ ሆነውም ገሠገሡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር በአዳራሾችዋ መጠጊያ ሆኖ ይታወቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተማይቱን ለማጥቃት ነገሥታት ኀይላቸውን አሰባሰቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጆሮዬ ምሳሌ አደምጣለሁ፥ በበገናም ነገሬን እገልጣለሁ። |
ይህም የሶርያን ንጉሥ እጅግ ስላበሳጨው፣ የጦር አለቆቹን ጠርቶ፣ “ከመካከላችን ከእስራኤል ንጉሥ ጋራ የተወዳጀ እንዳለ ለምን አትነግሩኝም?” ሲል ጠየቃቸው።
ከዚያ ሕዝብ ለሚመጡ መልእክተኞች ምን መልስ ይሰጣል? “መልሱ፣ ‘እግዚአብሔር ጽዮንን መሥርቷል፤ መከራን የተቀበለው ሕዝብም፣ በርሷ ውስጥ መጠጊያን አግኝቷል’ የሚል ነው።”
የዖዝያን የልጅ ልጅ፣ የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን፣ የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ ነገር ግን ድል ሊያደርጓት አልቻሉም።
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከርሱም ጋራ በፊቱ ምልክቶችን ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ። በእነዚህ ምልክቶች የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አሳተ። ሁለቱም በሕይወት እንዳሉ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ተጣሉ።