እንዲህ ስል ጸለይሁ፤ “አምላኬ ሆይ፤ ኀጢአታችን ከራሳችን በላይ ሆኗል፤ በደላችንም እስከ ሰማያት ደርሷል፤ አምላኬ ሆይ፤ ፊቴን ወደ አንተ ቀና ለማድረግ ፈራሁ፤ እጅግም ፈራሁ።
መዝሙር 38:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በደሌ ውጦኛል፤ እንደ ከባድ ሸክምም ተጭኖኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቁጣህ የተነሣ ሥጋዬ ጤና የለውም፥ ከኃጢአቴም የተነሣ አጥንቶቼ ሰላም የላቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደሌ በራሴ ላይ ተጭኖአል፤ እርሱም ለመሸከም ከምችለው በላይ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ” አልሁ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል ናቸው? ዐውቅ ዘንድስ ለምን ወደ ኋላ እላለሁ? |
እንዲህ ስል ጸለይሁ፤ “አምላኬ ሆይ፤ ኀጢአታችን ከራሳችን በላይ ሆኗል፤ በደላችንም እስከ ሰማያት ደርሷል፤ አምላኬ ሆይ፤ ፊቴን ወደ አንተ ቀና ለማድረግ ፈራሁ፤ እጅግም ፈራሁ።
“ኀጢአቶቼ ቀንበር ሆኑ፤ በእጆቹ አንድ ላይ ተገመዱ፤ በዐንገቴም ላይ ተጭነዋል፤ ኀይሌንም አዳከመ፤ ልቋቋማቸው ለማልችላቸው፣ እርሱ አሳልፎ ሰጠኝ።
ማንኛውም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ በሦስተኛው ቀን ከተበላ ተቀባይነት የለውም፤ ርኩስ በመሆኑ ላቀረበው ሰው ዋጋ አይኖረውም፤ ከዚያም የበላ ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል።