ከሕዝቡም ጋራ ከተመካከረ በኋላ ከሰራዊቱ ፊት ቀድመው በመሄድ፣ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና” እያሉ ለእግዚአብሔር የሚዘምሩና ስለ ቅድስናውም ክብር የሚያወድሱ ሰዎችን መደበ።
መዝሙር 29:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለስሙ የሚገባ ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤ በቅድስናው ግርማ ለእግዚአብሔር ስገዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የስሙን ክብር ለጌታ አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለጌታ ስገዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክብር ለእግዚአብሔር መሆኑን ግለጡ፤ በቅድስናና በግርማ ሞገስ ለተመላ አምላክ ስገዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ አምላኬ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ይቅርም አልኸኝ። |
ከሕዝቡም ጋራ ከተመካከረ በኋላ ከሰራዊቱ ፊት ቀድመው በመሄድ፣ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና” እያሉ ለእግዚአብሔር የሚዘምሩና ስለ ቅድስናውም ክብር የሚያወድሱ ሰዎችን መደበ።
ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ ከንጋት ማሕፀን፣ በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣ የጕልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ።
እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤ እርሷንም እሻለሁ፤ ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ውበት አይ ዘንድ፣ በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው።
ጨለማን ሳያመጣ፣ በሚጨልሙትም ተራሮች ላይ፣ እግሮቻችሁ ሳይሰናከሉ፣ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ። ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ፤ እርሱ ወደ ጨለማ ይለውጠዋል፤ ድቅድቅ ጨለማም ያደርገዋል።