መዝሙር 2:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድር ነገሥታት ተነሡ፤ ገዦችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ ላይ ሊመክሩ ተሰበሰቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በጌታና በመሢሑ ላይ ተማከሩ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርንና መሲሑን ለመቃወም የዓለም ነገሥታት ተነሣሡ፤ ሹሞቻቸውም ከእነርሱ ጋር ተባበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ ላይ እንዲህ ሲሉ በአንድነት ተሰበሰቡ። |
በርሱ ላይ ያሰማችሁትን ማጕረምረም ሰምቷልና በማለዳ የእግዚአብሔርን ክብር ታያላችሁ፤ ለመሆኑ በእኛስ ላይ የምታጕረመርሙት እኛ ምንድን ነንና ነው?” አሏቸው።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።
ሄሮድስ ጠቢባኑ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ በጣም ተናደደ። ከጠቢባኑ በተነገረው መሠረት፣ ዕድሜያቸው ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን የቤተ ልሔምንና የአካባቢዋን መንደሮች ወንድ ልጆች ሁሉ ልኮ አስገደለ።
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤ እርሱም እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ስለ ነበረ በደረሰበት ሁሉ መልካም እያደረገ በዲያብሎስ ሥልጣን ሥር የነበሩትን ሁሉ ፈወሰ።