መዝሙር 18:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍላጻውን ሰድዶ በተናቸው፤ ታላቅ መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ። በረዶና የእሳት ፍምም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍላጻውን ከቀስቱ አስፈነጠረ፤ ጠላቶቹንም በተናቸው፤ በመብረቁም ብልጭታ አሳደዳቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአንደበቴ ቃል ያማረ ይሁን፤ የልቤ ዐሳብም ሁልጊዜ በፊቴ ነው አቤቱ ረድኤቴ መድኀኒቴም። |
እግዚአብሔር በሚነድድ ቍጣና በሚባላ እሳት፣ በወጀብና በነጐድጓድ፣ በበረዶም ድንጋይ፣ ግርማ የተሞላበትን ድምፁን ሰዎች እንዲሰሙ አድርጎ ያሰማል፤ ክንዱም ስትወርድ ያሳያቸዋል።
በሰራዊቱ ፊት፣ እግዚአብሔር ያንጐደጕዳል፤ የሰራዊቱ ብዛት ስፍር ቍጥር የለውም፤ ትእዛዙንም የሚያደርግ እርሱ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ፣ እጅግም የሚያስፈራ ነው፤ ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?
“እግዚአብሔር ከግብጽ አወጣቸው፤ ብርታታቸውም እንደ ጐሽ ብርታት ነው፤ ጠላቶች የሆኗቸውን ሕዝብ ያነክታሉ፤ ዐጥንቶቻቸውን ያደቅቃሉ፤ በፍላጾቻቸው ይወጓቸዋል።
እግዚአብሔርም የአሞራውያንን ነገሥታት በእስራኤል ፊት አሸበራቸው፤ በገባዖን እጅግ መታቸው፤ ወደ ቤትሖሮን በሚያስወጣውም መንገድ ሽቅብ ተከተላቸው፤ እስከ ዓዜቅና እስከ መቄዳም ድረስ አሳድዶ መታቸው።
ከእግዚአብሔር ጋራ የሚጣሉ ይደቃሉ፤ እርሱ ከሰማይ ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል። “ለንጉሡ ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”