መዝሙር 148:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፀሓይና ጨረቃ አመስግኑት፤ የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፀሐይና ጨረቃ፥ አመስግኑት፥ የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ፥ አመስግኑት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፀሐይና ጨረቃ አመስግኑት። የምትበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፀሐይና ጨረቃ ያመሰግኑታል፤ ከዋክብትና ብርሃን ሁሉ ያመሰግኑታል። |
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለቀንና ለሌሊት የወሰንሁትን ሥርዐት በማፋለስ ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዳይፈራረቁ ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፣
ወደ ሰማይ ቀና ብለህ ፀሓይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን፣ የሰማይ ሰራዊትንም ሁሉ በምትመለከትበት ጊዜ፣ ወደ እነርሱ እንዳትሳብና እንዳትሰግድላቸው፣ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ በታች ላሉ ሕዝቦች ሁሉ ድርሻ አድርጎ የሰጣቸውንም ነገሮች እንዳታመልክ ተጠንቀቅ።