መዝሙር 137:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳላስታውስሽ ብቀር፣ ኢየሩሳሌምን የደስታዬ ቍንጮ ባላደርግ፣ ምላሴ ከትናጋዬ ጋራ ትጣበቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባላስታውስሽ፥ ምላሴ በጉሮሮዬ ይጣበቅ፥ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺን ባላስታውስሽና ታላቅ ደስታዬ አድርጌ ባልቈጥርሽ ምላሴ ከትናጋዬ ይጣበቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ከፍ ያለ ነውና፥ የተዋረዱትንም ይመለከታልና፤ ትቢተኛውንም ከሩቁ ያውቀዋል። |
በሌላ ስፍራ ሺሕ ቀን ከመኖር፣ በአደባባይህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላል፤ በክፉዎች ድንኳን ከመቀመጥ ይልቅ፣ በአምላኬ ቤት ደጅ መቆም እመርጣለሁ።
“ድኾችና ችግረኞች ውሃ ይፈልጋሉ፤ ዳሩ ግን ምንም አያገኙም፤ ጕረሯቸው በውሃ ጥም ደርቋል። ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር እመልስላቸዋለሁ፤ እኔ የእስራኤል አምላክ አልተዋቸውም።
ይሁን እንጂ፣ ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን ሩጫዬንና የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎቴን ብፈጽም፣ ለእኔ ሕይወቴ ከምንም እንደማይቈጠር እንደ ከንቱ ነገር ናት።
በምንም ዐይነት መንገድ ዐፍሬ እንዳልገኝ ጽኑ ናፍቆትና ተስፋ አለ፤ ነገር ግን እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም በሕይወትም ሆነ በሞት ክርስቶስ በሥጋዬ እንዲከበር ሙሉ ድፍረት ይኖረኛል።