ከብዙ ጊዜ በኋላም በሦስተኛው ዓመት እንዲህ የሚል የእግዚአብሔር ቃል ለኤልያስ መጣለት፤ “ሄደህ ለአክዓብ ተገለጥ፤ እኔም በምድሪቱ ላይ ዝናብ አዘንባለሁ።”
መዝሙር 135:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ደመናትን ከምድር ዳርቻ ያስነሣል፤ መብረቅ ከዝናብ ጋራ እንዲወርድ ያደርጋል፤ ነፋሳትንም ከማከማቻው ያወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምድር ዳርቻ ደመናትን ያወጣል፥ በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋሳትንም ከመዛግብቱ ያወጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝናብ ያዘለ ደመናን ከምድር ዳርቻ ያመጣል፤ በዝናብ ጊዜ መብረቅ እንዲኖር ያደርጋል፤ ነፋስንም ከቦታው ያወጣዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤ |
ከብዙ ጊዜ በኋላም በሦስተኛው ዓመት እንዲህ የሚል የእግዚአብሔር ቃል ለኤልያስ መጣለት፤ “ሄደህ ለአክዓብ ተገለጥ፤ እኔም በምድሪቱ ላይ ዝናብ አዘንባለሁ።”
ድምፁን ባንጐደጐደ ጊዜ በሰማይ ውሆች ይናወጣሉ፤ ጉሙን ከምድር ዳርቻ ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርገዋል፤ መብረቅን ከዝናብ ጋራ ይልካል፤ ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።
ከአሕዛብ ከንቱ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለን? ሰማያትስ በራሳቸው ማካፋት ይችላሉን? አይ! አይችሉም፣ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ነህ፣ ስለዚህም ተስፋችን በአንተ ላይ ነው።
ድምፁን ባንጐደጐደ ጊዜ በሰማይ ውሆች ይናወጣሉ፤ ጉሙን ከምድር ዳርቻ ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርገዋል፤ መብረቅን ከዝናብ ጋራ ይልካል፤ ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።
የበልግ ዝናብ እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ ማዕበሉን ደመና የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ ለሰዎች በቂ ዝናብን፣ ለእያንዳንዱም የምድርን ተክል ይሰጣል።
ነፋስ ወደሚወድደው ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ፤ ነገር ግን ከየት እንደ መጣ፣ ወዴት እንደሚሄድም አታውቅም፤ ከመንፈስም የተወለደ ሁሉ እንደዚሁ ነው።”